የተቋሙ ራዕይ፣ Vision/ በ2017ዓ.ም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፈቃድና ቁጥጥርን በቴክኖሎጂ በማዘመን በአዲስ አበባ ከተማ ፐላኑን የጠበቀ ግንባታና ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መፍጠር፡፡ የተቋሙ ተልዕኮ /Mission/ አገልግሎትን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በመዘርጋት የሰው ሀብት ልማት፤ ስምሪትና አስተዳደር አገልግሎቶችን በመስጠት የአስፈጻሚ አካላትን የመፈጸም እና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ የክትትልና ድጋፍ አገልቶችን በመስጠት የሀብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ነው፡ የተቋሙን እሴቶች Values/ የህግ የበላይነት ፡ ቅድሚያ ለደህንነት (Salty First)! ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ግልፀኝነት! ተጠያቂነት፤ ቅንነት፡የቡድን ስራ፣ ለሙያ ክብር መስጠት፤ የዕሴቶች ትርጓሜ፡- የህግ የበላይነት ፡- የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚመራባቸውን ህጎች፡ ደንብና መመሪያ በጠበቀ መልኩ በዘርፉ እንዲተገበር ማድረግ፤ ቅድሚያ ለደህንነት (Safty First) ፡- በግንባታው እና በስራ ቦታ አካባቢ የሰውና የንብረት ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት፡- የደንበኞች ፍላጎትን መሰረት ያደረጋ ቀልጣፋ ፈጣን አገልግሎት መስጠት፡ ግልፀኝነት፡- ዘርፉ የሚመራበትን የአሰራር ግልፀኝነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሁሉም አካል መረጃዎችን የሚያገኝበት ሁኔታ መፍጠር፣ ተጠያቂነት፡- በኮንስትራክሽን ሙያ ላይ የተሰማሩ አመራርና ፈጻሚዎች የተጣለባቸውን የሙያ ኃላፊነት በእኔነት ስሜት እንዲሰሩ እና ሳይወጡ ሲቀር የሚጠየቁበት አግባብ መፍጠር: ቅንነት፡- በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የአገልጋይነትን ስሜት ተላብሶ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ! የቡድን ስራ፡- በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በጋራ ሰርቶ በጋራ ውጤት የማምጣት ባህልን ማስፈን፡ ለሙያ ክብር መስጠት፡- በተግባር አፈጻጸም ሂደት ሙያው የሚፈልገውን ስነምግባርና ኃላፊነት መሰረት በማድረግ አገልግሎት መስጠት ፡ ስትራቴጂካዊ መስኮችና ውጤታቸው/ Center of Excellence የአገልግሎት አሰጣጣችንን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ማሻሻል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማትና ፈቃድ አሰጣጥ፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ክትትልና ቁጥጥር፣ የውጭ ማስታወቂያ አገልግሎት፣ 1.5 የፅ/ቤቱ ተገልጋዮች እና ባለ ድርሻ አካላት የፅ/ቤቱ ተገልጋዮች 1. የአቃቂ/ቃ/ክ/ ከተማ ነዋሪዎች 2. አልሚዎች ( የሀገር ውስጥና የውጭ) 3. አማካሪዎች፤ ስራ ተቋራጮች፤ መሀንዲሶች እና ሌሎች የዘርፉ ማህበራት? 4. 4, መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (የሃይማኖት ተቋማት፡ ማህበራት....) 5. መንግስታዊ ተቋማት የአቃቂ ክ/ከ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት የመንግስት ሕንፃና ንብረት አስተዳደር ፅ/ቤት የአቃቂ ክ/ከ አስተዳደር የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት፤ የአቃቂ ክ/ከ አስተዳደር የቤቶች ፅ/ቤት 6. አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና ተቋማት...) 7. የግል ድርጅት I 8. የውስጥ የስራ ክፍሎች 1.52 የቢሮው ባለድርሻ አካላት 1. የአቃቂ ክ/ከ ፕላን ልማት ፅ/ቤት 2. አማካሪዎች፥ ስራ ተቋራጮች፤ መሀንዲሶች እና ሌሎች የዘርፍ ማህበራት፤ 3. የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት 4. የተለያዩ የሙያና የሲቪክ ማህበራት 5. የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት፡ የጥናትና ምርምር ተቋማት 6. የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ባለስልጣን 7. የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ 8. የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 1.5 የተቋሙና የተገልጋዩ መብትና ግዴታዎች 1.6.1 የደንበኛ መብቶች ስለ እገልግሎቶቹ ሙሉ መረጃ የማግኘት፤ የመጠቀምና የሚጠይቀውን ወጭማወቅ፤ ተገቢውን አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር ማስተካከያ መጠየቅ፤ ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት ማግኘትና መጠቀም፤ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ ማግኘት፤ ተገልጋዮች አገልግሎቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማወቅ፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያየት /ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍታሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ ማግኘት፤ ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አገልግሎት ማግኘት፡ በመ/ቤቱ ዕቅድ እና ግብረ-መልስ ላይ መሳተፍና አስተዋጽዖ ማድረግ፤ 1.6.2 የደንበኞች ግዴታ ሕጎችን እና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል፤ ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ፤ የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታን መከተልና ማሟላት፤ የመ/ቤቱን ሕግና ደንብ ማክበር፤ የአገልግሎት ክፍያ የመክፍል፤ 1.6.3 የተቋሙ ግድታ አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ ግብዓቶችን አሟልቶ መገኘት፣ ስለ አገልግሎቱ ሙሉ መረጃ እና ምክር መስጠት፤ በአገልግሎት ውስጥ ህብረተሰቡን ማሳተፍ፤ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት መስጠት፤ ለተገልጋይ ህብረተሰብ ፍትሃዊ አድሎ የሌለበት እና እኩልነትን የተላበሰ አገልግሎት መስጠት፤ ደንበኞች የሚሰጡትን ቅሬታ መቀበል፤ ደንበኞች በተቋሙ ምዘና እንዲሳተፉ ማድረግ፤ ለደንበኞች የሚሰጡ ምላሾች በዝርዝር በጽሁፍ መስጠት፤ 1.7 ለተገልጋዮች የምንገባው ቃል በቻርተሩ በተቀመጠው የአገልግሎት አሠጣጥ ስታንዳርድ መሠረት ለዜጎች አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ ሕግ እና የመንግስትን ፖሊሲ ተከትለን ስራችንን እንተገብራለን፡፡ ዜጎችን በአክብሮት በፍትሃዊነት እና ያለአድሎ እናገለግላለን፡፡ የብልሹ አሰራር እና የሌብነት አመለካከት እና ተግባርን አጥብቀን እንታገላለን፤ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች(ሴቶች፣ ኅጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን ወዘተ) ልዩ ትኩረት ሰጥተን እናገለግላለን፡፡ ተገልጋዮች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን፤ ለሰጠናቸው አገልግሎቶች ለወሰናቸው ውሳኔዎች ተጠያቂ ነን፡፡ በፅቤቱ በጥቅሉ 5 ዋና አገልግሎቶችና በስራቸውም 29 ዝርዝር አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን እነዚህም እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡ 2.2.1 ዋና ዋና አገልግሎቶች የመረጃ መስጠት አገልግሎት የህንፃ ግንባታ ፈቃድ አገልግሎት የውጪ ማስታወቂያ ፈቃድ አገልግሎት የህንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር አገልግሎት 1. የመረጃ መስጠት አገልግሎት 1. ተቋማዊ የአንድ ማዕከል የኮፒ መረጃ መስጠት አገልግሎት 2. የተፈቀዱ ፍቃዶችን በጂአይኤስ ማወራረስና በማደራጀት ለሚመለከተው ማስተላለፍ 3. የግንባታ ደረጃ መስክ ሪፖርት መረጃ መስጠት አገልግሎት 2. የህንፃ ግንባታና ፈቃድ አገልግሎት • የፕላን ስምምነት መረጃ መስጠት አገልግሎት • የአዲስ ህንፃ ግንባታ ፈቃድ አገልግሎት • የማሻሻያ ፈቃድ አገልግሎት • የስምና የአገልግሎት ለውጥ ፈቃድ መስጠት • የአስቢዩልት ፈቃድ አገልግሎት • የእድሳት ፈቃድ አገልግሎት • የአጥር ግንባታ ፈቃድ አገልግሎት • የግንባታ ማፍረሻ ፈቃድ አገልግሎት • የጊዜያዊ ግንባታ ፈቃድ አገልግሎት • የምሽት ግንባታ ፈቃድ አገልግሎት የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር አገልግሎት • የግንባታ ማስጀመሪያ ጊዜ ማራዘሚያ ፈቃድ አገልግሎት • የግንባታ ማስጀመሪያ ፈቃድ አገልግሎት • የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ማራዘሚያ ፈቃድ አገልግሎት • የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር አገልግሎት የህንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት • የህንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ መስጠት የውጪ ማስታወቂያ ፈቃድ አገልግሎት • የውጪ ማስታወቂያ ሰሌዳ መትከያ ቦታ መምረጥ፣ ማጽደቅ እና በጨረታ የማስተላለፍ አገልግሎት • የውጪ ማስታወቂያ ሰሌዳ የመትከል ሥራ ክትትልና ቁጥጥርአገልግሎት