የህግ የበላይነት ፡- የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚመራባቸውን ህጎች፡ ደንብና መመሪያ በጠበቀ መልኩ በዘርፉ እንዲተገበር ማድረግ፤ ቅድሚያ ለደህንነት (Safty First) ፡- በግንባታው እና በስራ ቦታ አካባቢ የሰውና የንብረት ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት፡- የደንበኞች ፍላጎትን መሰረት ያደረጋ ቀልጣፋ ፈጣን አገልግሎት መስጠት፡ ግልፀኝነት፡- ዘርፉ የሚመራበትን የአሰራር ግልፀኝነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሁሉም አካል መረጃዎችን የሚያገኝበት ሁኔታ መፍጠር፣ ተጠያቂነት፡- በኮንስትራክሽን ሙያ ላይ የተሰማሩ አመራርና ፈጻሚዎች የተጣለባቸውን የሙያ ኃላፊነት በእኔነት ስሜት እንዲሰሩ እና ሳይወጡ ሲቀር የሚጠየቁበት አግባብ መፍጠር: ቅንነት፡- በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የአገልጋይነትን ስሜት ተላብሶ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ! የቡድን ስራ፡- በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በጋራ ሰርቶ በጋራ ውጤት የማምጣት ባህልን ማስፈን፡ ለሙያ ክብር መስጠት፡- በተግባር አፈጻጸም ሂደት ሙያው የሚፈልገውን ስነምግባርና ኃላፊነት መሰረት በማድረግ አገልግሎት መስጠት ፡