በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ......

ዝርዝር ዜና

ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ፅ/ቤት
no photo

በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት የተሰሩ አበይት ስራዎች!!

ሰኔ 24-2017

የከተማን ስታንዳርድ የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት ከደንብ ማስከበርና ሰላምና ፀጥታ ጋር በመቀናጀት ከተማን የማስዋብና ስታንዳርድ የማስጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል። የፅ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔ እንደገለፁት ከተማን ውብ ፅዱ ስታንዳርዷን የጠበቀች ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት በመሆኑ ሁሉም ህንፃውን ማስዋብና የግንባታ ግብአቶችን ከመንገድ ላይ ማንሳት ፤ዲጂታል የሆኑ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ማስታወቂያዎችን ብቻ መጠቀምና ለከተማችን ውበት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።