በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ......

ዝርዝር ዜና

ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ፅ/ቤት
no photo

በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት የተሰሩ አበይት ስራዎች!!

ሰኔ 25-2017

በሀሰተኛ ሰነድ የሚደረግ ህገ-ወጥ ግንባታን ለመከላከል የበለፀገ ሲስተም ሙሉ ለሙሉ ወደ ተግባር መግባቱ ተገለፀ ። የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ ) የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ከኢኖቬሽን ቢሮ ጋር በመቀናጀት ያበለፀገውን አዲስ የCPCS ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ማስገባት የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሂዷል። በመርሀሃ-ግብሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የክ/ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔን ጨምሮ የሁሉም ወረዳዎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቴክኖሎጂው ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ገብቷል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ክ/ከተማው ከዚህ ቀደም በርካታ ቴክኖሎጂዎችን በማልማት መደ ስራ ያስገባ መሆኑን አንስተው በዛሬው ዕለት በሙሉ አቅም ወደ ስራ የገባው ቴክኖሎጂ ህገ-ወጥነት፣ ሌብነትንና የውሸት ሪፖርቶችን የሚያስቀር እንዲሁም ስራዎችን የሚያዘምንና የሚያቀላጥፍ ለተቋም ግንባታ ቁልፍ የሆነ ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቴክኖሎጂው ወደ ስራ ገብቶ ውጤት እንዲያመጣ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የክ/ከተማው የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔ በበኩላቸው የበለፀገው የCPCS ሲስተም የተገልጋይ ምሬትንና ህገ-ወጥ ተግባረትን የሚቀንስ ፣ የሚባክን የመንግስት ሀብትን የሚቆጣጠር መሆኑን ጠቅሰው ቴክኖሎጂው ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። በመርሀ-ግብሩ የCPCS ሲስተም አጠቃላይ የሚሰጠው አገልግሎትና አጠቃቀም በአቶ ጌታሰው አበበ የቀረበ ሲሆን ቴክኖሎጂው እንዲበለፅግ የበኩላቸውን ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቷል።