የከተማ ስታንዳርዳይዜሽንን የማስጠበቅ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ተገምግመው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀመጠ °°° ሚያዚያ 30/2017 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት የከተማ ስታንዳርዳይዜሽንን የማስጠበቅ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ከዘርፍ ኃላፊዎችና የስራ አስተባባሪዎች በተገኙበት ተገምግመው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል። የአዲስ አበባ ከተማ ለዜጎች ምቹና ሳቢ እንድትሆን ወደ ተግባር ከተገባ ጊዜ ጀምሮ የከተማዋን ስታንዳርዳይዜሽን ለማስጠበቅ በክፍለ ከተማው በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዛሬው ዕለትም፣ከከተማ በተገኘ ቡድን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔ፣የወረዳ የዘርፍ አመራሮችና የክፍለ ከተማው የሥራ አስተባባሪዎች በተገኙበት የከተማ ስታንዳርዳይዜሽንን የማስጠበቅ ስራዎች ያሉበት ደረጃ፣ እስከ አሁን የተከናወኑ ተግባራትን በመረጃ ማደራጀትና፣የቀሩ ስራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፤ለተግባራዊነታቸውም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።