የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አቻው ልምድ አካፈለ °°° የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አቻው ልምድ አካፈለ። በልምድ ልዉዉጡ፣የሰነድ አያያይዝ፣የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት አዲስ ያበለጸገውን ሲስተም ምልከታ፣የወጪና የገቢ ደብዳቤዎች አያያዝ፣የፍቃድ ፕሮቶኮል መዝገብ አያያዝና ሌሎች ሰነዶችን ተመልክተዋል። ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት የመጡ አካላት ከክፍለ ከተማው በርካታ ልምዶችን ወስደው፣በተለይም አዲሱን ሲስተም ወደ ተቋም ለመቀየር ልምድ ልዉዉጡ እጅግ ወሳኝ እንደነበር ገልጸዋል። በተጨማሪም ለልምድ ልዉዉጥ የመጡት አካላት፤ ጽህፈት ቤቱ የከተማዋን ስታንዳርዳይዜሽን ለማስጠበቅ የኮሪደር ልማት፣የህንጻዎች ቀለም ቅየራ፣የዉስጥ ለዉስጥ ብሎኪንግ አሰራርን በሰነድ ተመልክተዋል። ግንቦት 1 ፤2017 -[የአቃ/ቃ/ክ/ግንባታ/ፍ/ቁጥጥር መረጃ ማዕከል]