የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት በግንባታ ክትትል ወቅት ለሴፍቲ የሚዉሉ ሄልሜት እና የአንጸባራቂ አልባሳት ስርጭት ለጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች አበርክቷል °°° የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት በግንባታ ክትትል ወቅት ለሴፍቲ የሚዉሉ ሄልሜት እና የአንጸባራቂ ስርጭት ለጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች አበርክቷል። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔ ፤ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ሪፎርም ከተደረጉ ጽህፈት ቤቶች መካከል መሆኑን ገልፀው፥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በቅርቡ ወደ ስራ ማስገባቱንና ዛሬም የሪፎርም አካል የሆነው፣ የሴፍቲ አልባሳትን ለጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ማሰራጨቱንም ተናግረዋል። ዛሬ የተሰጡት የሄልሜት (Hard hat) እና አንጸባራቂ አልባሳት (visibility safety vest)በዋናነት ደህንነትን ከመጠበቅ ዓላማው ባሻገር የጽህፈት ቤቱን ሰራተኞች ከሌሎች አካላት መለየት የሚያስችል እንደሆነም ገልፀዋል። ግንቦት 18|2017 -( የአቃ/ቃ/ክ/ግንባ/ፍ/ቁጥጥር መረጃ ማዕከል)