በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ......

ዝርዝር ዜና

ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ፅ/ቤት
no photo

በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት የተሰሩ አበይት ስራዎች!!

ሰኔ 25-2017

በይቻላል መንፈስ የግንባታ ቦታ ደህንነትን እናስጠብቅ👷‍♀️👷‍♂️ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በመገንባት ሂደት ላይ ያሉ ህንጻዎች በከተማዋ ስታንዳርድ መሠረት ድህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ 👷‍♀️👷‍♂️👷‍♀️👷‍♂️👷‍♀️ በህንጻዎች ግንባታ ወቅት የሚያጋጥሙ የድህንነት ጉዳቶችን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት በጽህፈት ቤቱ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል። የሚሰሩ ህናጻዎች የደህንነት ቅድመ-ሁኔታን አሟልተው እንዲሰሩና በመገንባት ላይ ያሉ ህንጻዎችም ድህንነታቸው እንዲጠበቅ፣የህንጻ ባለቤቶችም ህንጻን በሚያስገነቡበት ወቅት የሰራተኞችን ድህንነት በጠበቀ መልኩ አስፈላጊው የድህንነት አልባሳትን አሟልተው እንዲሆን ህንፃዎች ተሸፍነው እንዲሰሩ ለማስቻል በተቀናጀ መልኩ ግንዛቤ እየተሰጠና የመስክ ጉብኝት እየተደረገ ይገኛል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔ የግንባታ ቦታ ደህንነት ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ደህንነት መጠበቅ በመሆኑ በትኩረት እንዲከናወን ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ላሉ ኃላፊዎችና ባለ-ሙያዎች የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ግንቦት 06 ቀን 2017 ዓ.ም (የአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ግን/ፍ/ቁ ሚዲያ ማዕከል)