የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ከዛሬ ሰኔ 25......

ዝርዝር ዜና

ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ፅ/ቤት
no photo

የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ከዛሬ ሰኔ 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5/2017 ድረስ የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ተሻሻለ!!

ሰኔ 25-2017

ለዉድ የተቋማችን አግልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ!* የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ቀልጣፋ ፤ ተደራሽ እንዲሁም የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ከዛሬ ሰኔ 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ድረስ እንደተቋም በወረደው አቅጣጫ መሰረት አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናችን እንገልፃለን ፡፡ በዚህም መሰረት * ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 2፡30 እስከ ምሽት 2፡00 * ቅዳሜ ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 * እሁድ ከጠዋት 2፡30 እስከ 6፡30 እስከ ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ተጨማሪ የስራ ሰዓት ሁኖ ተገልጋዩን ማህበረሰብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አግልግሎት ማግኘት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን፤ ከዛሬ 25/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለመደውን አገልግሎት በተቋሞቻችን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በድጋሚ ከታላቅ አክብሮት ጋር እናሳዉቃለን!! በተሻሻለ የስራ ባህል የህብረተሰባችንን እርካታ እናረጋግጣለን !! የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት !!