ታላቅ የምስራች ከወደ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ተሰማ !! እንኳን_ደስ_አላችሁ! ዉጤትን ልማድ ያደረገዉ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በዛሬዉ እለትም “ ህዝብን ማገልገል ክብር ነው !” በሚል መሪ ቃል የተነሳው የክ/ከተማዉ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት አጠቃላይ አፈፃፀም በከተማ አስተዳደሩ ስር ከሚገኙ 11 ክ/ከተሞች መካከል 1ኛ ደረጃ በመዉጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ። አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስታወት ደጀኔ ከፈኒ በተገኘዉ ዉጤት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ይህ ዉጤት እንዲመጣ የበኩላቸዉን አስተዋፅዖ ላበረከቱ የክ/ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ አጠቃላይ አመራሮች፣ ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች እና የተቋሙ ባለድርሻ አካላት በተቋሙ ስም ከልብ አመስግነዋል። "አልቆ ለመፈፀም ከህዝብ የተሰጠን አደራ!" ነሀሴ 01/2017 ዓ.ም