የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎች የአቃቂ ቃሊቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየው ሚጀና በተገኙበት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት በመገኘት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን በመቃኘት በቀጣይ ጊዜያት መከወን ያሉባቸውን ተግባራት ላይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ የአቃቂ ቃሊቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየው ሚጀና ለአገልግሎት አሰጣጡ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ህይወት ሳሙኤል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት በመገኘት ከፅ/ቤቱ አጠቃላይ ሰራተኛና ከወረዳ አመራሮች ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን ፅ/ቤቱ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያለባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበው ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመታገል አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ሰኔ 9/2017