በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ግ......

ዝርዝር ዜና

ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ፅ/ቤት
no photo

በ2017 በጀት አመት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የተሰሩ ስራዎች

ሰኔ 23-2017

በሁሉም ወረዳዎች ወጥ የሆነ አሰራር ለማምጣትና አሰራር ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። 👷‍♂️👷👷‍♂️👷👷‍♂️👷👷‍♂️👷👷‍♂️👷👷‍♂️👷 የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት በየ 15 ቀኑ በየወረዳዎች በመዘዋወር መመሪያዎች የማሰልጠንና የስራ ቦታን የመጎብኘት ተግባር እያከናወነ ይገኛል።በዚህም ወረዳ 8 እና 7 ላይ የተገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች እንደገለፁት የተሻለ መቀራረብና ልምድ የተለዋወጥንበት ስለሆነ በዚሁ ይቀጥል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ሀላፊ መስታወት ደጀኔ የወጡ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ልምድ ለመለዋወጥና ተግባራትን በውጤት ለማጠናቀቅ ይህ አይነቱ ልምድ ጠቃሚ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።